







የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአዲስ አበባ ባደረገው ቆይታ ከፌዴራል እና ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
በዚህ ሳምንት በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ ከፌዴራል መንግስት፣ ከፌደራል ኤጀንሲዎች እና ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተወያየባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች የትግራይ ህገ-መንግስታዊ አስተዳደር መልሶ ማቋቋም፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ እና ማቋቋም፣ የታገደው የትግራይ አመታዊ በጀት እንዲፈታ እና የትግራይን መልሶ መገንባት ይገኙበታል።
በቆይታቸውም ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትግራይ መልሶ ግንባታ እና ማገገም ላይ ያተኮሩ ከተለያዩ የፌዴራል ኤጀንሲዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
You must log in to post a comment.