* የትግራይ ሰራዊት ብቃት መግለፅ ኣይጠበቅብኝም፣ ለህልውናው የሚታገል ብቃት ያለው ሰራዊት ነው።
* እቶቼ ወንድሞቼ፣ ኣባቶቼ እናቶቼ ክብሬ ኣሳልፌ ኣልሰጥም ያለ ሰራዊት ነው።
* በትግራይ ላይ የተቀሰሩ ጣቶች እንዲቆጠቡ የተሰማራ ሰራዊት ነው። ስለ ሰራዊቱ ሚልየን ብንናገር የሚበቃ ኣይመስለኝም።
* በጦርነት ሊዘጉት ያልቻሉትን ጉሮሮ በመብራት፣ በስልክ በመንገድ መዝጋት ሊተገብሩት እየጣሩ ነው።
* ኣማራ ክልል የገባነው እነ ኣገኘሁ እና ኣብይ እንደሚያወሩት ሳይሆን፣ በትግራይ እናቶች የተቀሰሩ ጣቶች ለማስታገስ ነው።
* በገባንባቸው የኣማራ ክልል ከተሞች ህዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር እያደረግን ነው።
* በገባንባቸው ከተሞች ህዝቡ በደስታ እየተቀበለን ነው፣ በደስታ የሚቀበለን እንደግል ኣዳኝ ቆጥሮን ኣይደለም እህቶቹ እናቶቹ ላይ ሲተኩስ ስላላየው ነው።
* እነ ኣብይ እና ኣገኘሁ ኣንዳንዴ እንደ ኣሸማጋይ፣ ኣንዳንዴ ነብያት ሁነው ለመኖር ነው የሚፈልጉት ግን ኣንፈቅድላቸውም።
* ላሊበላ ስንገባ ላሊበላን እንዳትነኩ ብለው የጠየቁ ኣሉ፣ ስለ ኣክሱም እና ስለ ኣልነጃሺ የተናገረ ግን ማንም ኣልነበረም።
* የትግራይ ሰራዊት ስም ለማጉደፍ እና ታሪካቸውንም ጭምር ምንም ስለ ማይመስላቸው ራሳቸውም ሊመቱት ይችላሉ።
* ህዝቡ የምትፈልጉዋቸው ወንበዴዎች ካሉ ንገሩን ራሳችን መንጥረን እንሰጣቹሃለን እያለን ነው።
* በገባንበት ሁሉ ጠብመንጃው ጭራሮ ኣስመስሎ እየተወያየ ነው።
* ራያና ወልቃይት ከተያዘ ራሴን ኣጠፋለሁ ያለው ኣገኘሁ ተሻገር ኣሁን ወደ ስልጣኔን እለቃለሁ የሚል ቀይሮታል።
* ወልድያ ውግያ እየተካሄደ ቆቦ ይልሻል፣ ጨጨሆ ውግያ እየተደረገ ወልድያ ይልሻል። በዚህ ነው ልሸውዱት የሚፈልጉት።
* እነዚህ ቅርሻቶች ለዚህ ህዝብ እያስተዳድሩ ስታይ ፣ እነዚህ እንዲፈጠሩ ኣስተዋፅኦ ማድረግህ ይቆጭሃል።
* ብልፅግና በራያ ግንባር እያለ ይፎክራል፣ ራያ ግንባር ወፍ የለም።
* ለምንድነው የሚዋሹት? ውሸት የስራቸው ኣልፋና ኦሜጋ ስለሆነ ነው።
* የኣማራ ወጣት የማይክል ጃክሰን they don’t really care about us የሚለውን ዘፈን ሰምተው ለነ ደመቀ ይህንን ነው ማለት ያለባቸው።
* ኣወል ኣርባ የኣብይ የሳሎን ውሻ ነው፣ የኣብይ ፈገግታ ካየ በቃ በዛው ይረካል።
* ዓፋር ክልል ላይ ያለው ጋሊኮማ ኣይደል 10 ሺ ተፈናቃይ፣ እዛ ኣከባቢ 10 የሚያህል ኗሪ የለም።
* ዓፋር ውስጥ ያሉ ወጣቶች ኣታግሉን ነው እያሉን ያሉት።
* ህፃን ኣይገደልብኝ ብሎ የተነሳ ሰራዊት ህፃን በመግደል ትግሉን ኣያሳካም።
* ኣብይ መንግስቱ ሃይለማርያም ለመምሰል የነበረው ፍላጎት በተሟላ መልኩ እየተገለፀበት ያለ ሁኔታ ነው ያለው። መልካቸው ሳይመሳሰል ኣይቀርም ኣሁን።
* ምዕራብ ትግራይ ነፃ እናወጣዋለን። እነሱ ስለ ማይችሉት ለሻዕቢያ ሊሰጡት እየተደራደሩ ናቸው። ሻዕቢያ ይግባ እናሳየዋለን።
* የኣማራ ልዩ ሃይል እየተዋጋ መከላከያ ወደ ኃላ እየሸሸ ብለው ነው የሚያወሩት ፣ ሁሉም እየተዋጉ እየቀጣናቸው ነው ያሸነፍነው።
* የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የቀረው ታንኩ፣የቀረው ሮኬቱ፣የቀረው መድፉ፣ የቀረው ኣሻንጉሊቱ ይዞ ተዋግቷል። ተሟርካል።
* ኣዳዲስ የጦር መሳርያ እየገዛ እንደሆነ መረጃው ኣለን፣ ድሮንም፣ታንክም፣ ዲሽቃም መድፍም እየገዛ ነው፣ እናውቃለን።
* ክተት የተባለው የዘር ማጥፋት ድርጊቱ ህዝባዊ ተሳትፎ እንዲኖረው ተፈልጎ የተሰራ ነው።
* የትግላችን ኣልፋና ኦሜጋ የትግራይ ህዝብ መብት ማስከበር ነው።
* የሰሜን እና የደቡብ ዕዝ ኣዛዦች ክንዱ በዙ፣ ሰለሞን ኢተፋ ላሊበላ ላይ፣ ወልድያ ላይ ምን ሲሰሩ ነበር ብለው ይጠይቋቸው፣ ካገኙዋቸው።
* ተኩስ ኣቁም ላይ ነበርኩ የሚለው ኣብይ፣ ሰራዊቱ ደብረ ዘቢጥ፣ ጨው በር፣ ዓዲ ኣርቃይ፣ ወልድያ ከነ ታንኩ ምን ሲሰራ ነበር?
* እኔ ከሞትኩ ሰርዶ ኣይብቀል የሚለው ለኣህያ ተሰጣት እንጂ፣ ይህንን ድርጊት ለኣብይ ነው የሚገልፀው።
* መወልወያ እና ‘መሽረፈት’ የሚሸጡ የትግራይ ተወላጆች ተግፈተዋል።
* እየሸሸህ መማረክ ኣትችልመ፣ እየተገረፍክ እንዴት ነው የምትማርከው? ሳትዋጋ እንዴት ነው የምትማርከው።
* ብዙዎች እየተጠነቀቃችሁ ከኣብይ መቃብር ብትርቁ መልካም ነው።
ቴሌቪዥን ትግራይ 05 ሓምሌ 05/2013 ኣቆፃፅራ ግዕዝ
Via Kibrom Mulugeta
You must be logged in to post a comment.