አትሌት ደራርቱ ቱሉ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች በማንነታቸው ምክንያት ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ካጠገባቸው በመሆን የችግራቸውን ተካፋይ ከመሆን አልፋ ያጋጠማቸውን ችግር በመፍታት አትሌቶቻችን ለድል ማብቃት በመቻልዋ በትግራይ ህዝብ እና መንግስት ትመሰገናለች” ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚኬኤል


በአትሌት ደራርቱ ቱሉ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌደረሽን ልኡክ እና አትሌቶች ከትግራይ ፕረዚዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ደራርቱ ከመጀመርያውም ጀምሮ ብዙ ሰው በሸሸበት ጌዜ ግልፅ የሰላም አቋም በመያዝ ሁኔታው በሰላም እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ መጥታለች ያሉት ዶክተር ደብረፅዬን አትሌት ደራርቱ ቱሉ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች በማንነታቸው ምክንያት ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ካጠገባቸው በመሆን የችግራቸውን ተካፋይ ከመሆን አልፋ ያጋጠማቸውን ችግር በመፍታት አትሌቶቻችን ለድል ማብቃት በመቻልዋ በትግራይ ህዝብ እና መንግስት ትመሰገናለች ብሏል።
የትግራይ ህዝብ እና መንግስትም ከመጀመርያ ጀምረው ስለ ሰላም ከፍተኛ ዋጋ ከፍለናል አሁንም ህዝባችን በውጭ ወረራሪ ሃይሎች እየተጨፈጨፈም የሰላም አቋማችን የፀና ነው…ሰላሙ አሁንም አጠናክረን እቀጥልበታለን በማለት ተናግሯል።
ሙሉብርሃን ግደይ








